ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 22:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. መልካም ስም ከብዙ ብልጽግና ይመረጣል፤መከበርም ከብርና ከወርቅ ይበልጣል።

2. ባለጠጋና ድኻ የሚጋሩት ነገር፣ እግዚአብሔር የሁላቸውም ፈጣሪ መሆኑ ነው።

3. አስተዋይ ሰው አደጋ ሲያይ መጠጊያ ይሻል፤ብስለት የጐደለው ግን በዚያው ይቀጥላል፤ መከራም ያገኘዋል።

4. ትሕትናና እግዚአብሔርን መፍራት፣ሀብትን፣ ክብርንና ሕይወትን ያስገኛል።

5. በክፉዎች መንገድ ላይ እሾህና ወጥመድ አለ፤ነፍሱን የሚጠብቅ ግን ከእነዚህ ይርቃል።

6. ልጅን የሚሄድበትን መንገድ አስተምረው፤በሚሸመግልበት ጊዜ ከዚያ ፈቀቅ አይልም።

7. ባለጠጋ ድኻን ይገዛል፤ተበዳሪም የአበዳሪ ባሪያ ነው።

8. ክፋትን የሚዘራ መከራን ያጭዳል፤የቊጣውም በትር ይጠፋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 22