ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 21:24-30 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው፣ ኋፌዘኛቃ ይባላል፤በጠባዩም እብሪተኛ ነው።

25. ታካችን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።

26. ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።

27. የክፉ ሰው መሥዋዕት አጸያፊ ነው፤በክፉ ዐላማ ሲያቀርብማ የቱን ያህል አስከፊ ይሆን!

28. ሐሰተኛ ምስክር ይጠፋል፤እውነቱን የሚናገር ግን ጸንቶ ይኖራል።

29. ክፉ ሰው በዐጒል ድፍረት ይቀርባል፤ቅን ሰው ግን አደራረጉን ያስተውላል።

30. እግዚአብሔርን ለመቋቋም የሚያስችል፣አንዳችም ጥበብ ማስተዋልና ዕቅድ የለም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 21