ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 21:20-26 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. በጠቢብ ቤት ምርጥ ምግብና ዘይት ተከማችቶ ይገኛል፤ተላላ ሰው ግን ያለ የሌለውን ያሟጥጣል።

21. ጽድቅንና ፍቅርን የሚከተል፤ሕይወትን ብልጽግናንና ክብርን ያገኛል።

22. ጠቢብ የኀያላንን ከተማ ቅጥር ጥሶ ይገባል፤መታመኛ ምሽጋቸውንም ያፈርሳል።

23. አንደበቱንና ምላሱን የሚቈጣጠር፣ራሱን ከመቅሠፍት ይጠብቃል።

24. ትዕቢተኛና ኵሩ ሰው፣ ኋፌዘኛቃ ይባላል፤በጠባዩም እብሪተኛ ነው።

25. ታካችን የሚገድለው ምኞቱ ነው፤እጆቹ መሥራት አይፈልጉምና።

26. ክፉ ሰው ቀኑን ሙሉ ይመኛል፤ጻድቅ ግን አንዳች ሳያስቀር ይሰጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 21