ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 20:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. ወርቁም አለ፤ ቀዩም ዕንቊ ተትረፍርፎአል፤ዕውቀት የሚናገሩ ከንፈሮች ግን ብርቅ ጌጦች ናቸው።

16. ለማይታወቅ ሰው ዋስ የሆነውን ልብሱን ግፈፈው፤ለዘልዛላ ሴት የተዋሰውን በቃሉ ያዘው።

17. ሰው በማጭበርበር ያገኘው ምግብ ይጣፍጠዋል፤በመጨረሻ ግን አፉን ኰረት ሞልቶት ያገኘዋል።

18. ምክር ጠይቀህ ዕቅድ አውጣ፤ጦርነት የምትገጥም ከሆነ መመሪያ ተቀበል።

19. ሐሜተኛ ምስጢር ያባክናል፤ስለዚህ ለፍላፊን ሰው አርቀው።

20. አባቱን ወይም እናቱን የሚሰድብ፣መብራቱ በድቅድቅ ጨለማ ይጠፋል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 20