ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 19:9-19 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ሐሰተኛ ምስክር ከቅጣት አያመልጥም፤ውሸት የሚነዛም ይጠፋል።

10. ተላላ ተንደላቆ መኖር አይገባውም፤ባሪያ የመሳፍንት ገዥ ከሆነማ የቱን ያህል ይከፋ!

11. ጥበብ ሰውን ታጋሽ ታደርገዋለች፤በደልን ንቆ መተውም መከበሪያው ነው።

12. የንጉሥ ቊጣ እንደ አንበሳ ግሣት ነው፤በፊቱ ሞገስ ማግኘትም በሣር ላይ እንዳለ ጠል ነው።

13. ተላላ ልጅ ለአባቱ መጥፊያ ነው፤ጨቅጫቃ ሚስትም እንደማያቋርጥ ጠፈጠፍ ናት።

14. ቤትና ሀብት ከወላጆች ይወረሳሉ፤አስተዋይ ሚስት ግን ከእግዚአብሔር ዘንድ ናት።

15. ስንፍና ከባድ እንቅልፍ ላይ ይጥላል፤ዋልጌም ሰው ይራባል።

16. ትእዛዛትን የሚያከብር ሕይወቱን ይጠብቃል፤መንገዱን የሚንቅ ግን ይሞታል።

17. ለድኻ የሚራራ ለእግዚአብሔር ያበድራል፤ስላደረገውም ተግባር ዋጋ ይከፍለዋል።

18. ገና ተስፋ ሳለ፣ ልጅህን ሥርዐት አስይዘው፤ሲሞት ዝም ብለህ አትየው።

19. ግልፍተኛ ሰው ቅጣትን መቀበል ይገባዋል፤በምሕረት ካለፍኸው ሌላም ጊዜ አይቀርልህም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 19