ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 19:23-28 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. እግዚአብሔርን መፍራት ወደ ሕይወት ይመራል፤እንዲህ ያለውም ሰው እፎይ ብሎ ያርፋል፤ መከራም አያገኘውም።

24. ሰነፍ እጁን ከወጭቱ ያጠልቃል፤ወደ አፉ ግን መመለስ እንኳ ይሳነዋል።

25. ፌዘኛን ግረፈው፤ ብስለት የሌለውም ማስተዋልን ይማራል፤አስተዋይን ዝለፈው፤ ዕውቀትን ይገበያል።

26. አባቱን የሚዘርፍ፣ እናቱንም የሚያሳድድ፣ዕፍረትና ውርደት የሚያመጣ ልጅ ነው።

27. ልጄ ሆይ፤ እስቲ፣ ምክርን ማዳመጥ ተው፤ከዕውቀትም ቃል ትስታለህ።

28. ዐባይ ምስክር በፍትሕ ላይ ያፌዛል፤የክፉዎችም አፍ በደልን ይሰለቅጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 19