ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 18:8-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤ወደ ሰው ውስጣዊ ክፍል ዘልቆ ይገባል።

9. ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣የአጥፊ ወንድም ነው።

10. የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።

11. የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤እንደማይወጣ ረጅም ግንብም ይቈጥሩታል።

12. ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።

13. ከማዳመጡ አስቀድሞ የሚመልስ፣ቂልነትና ዕፍረት ይሆንበታል።

14. በሕመም ጊዜ፣ ሰውን መንፈሱ ትደግፈዋለች፤የተሰበረውን መንፈስ ግን ማን ሊሸከም ይችላል?

15. የአስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይገበያል፤የጠቢብም ጆሮ አጥብቆ ይሻታል።

16. እጅ መንሻ ለሰጪው መንገድ ትከፍትለታለች፤ታላላቅ ሰዎች ፊትም ታቀርበዋለች።

17. አስቀድሞ ጒዳዩን የሚያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ይኸውም ባላንጣው መጥቶ እስከሚመረመር ድረስ ነው።

18. ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 18