ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 18:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ተላላ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

8. የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤ወደ ሰው ውስጣዊ ክፍል ዘልቆ ይገባል።

9. ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣የአጥፊ ወንድም ነው።

10. የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።

11. የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤እንደማይወጣ ረጅም ግንብም ይቈጥሩታል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 18