ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 18:4-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።

5. ለክፉ ሰው ማድላት፣ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።

6. የተላላ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤አፉም በትር ይጋብዛል።

7. ተላላ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 18