ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 18:2-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

2. ተላላ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል።

3. ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ከዕፍረትም ጋር ውርደት ትመጣለች።

4. ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።

5. ለክፉ ሰው ማድላት፣ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።

6. የተላላ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤አፉም በትር ይጋብዛል።

7. ተላላ ሰው አፉ መጥፊያው ነው፤ከንፈሮቹም ለነፍሱ ወጥመድ ናቸው።

8. የሐሜተኛ ቃል እንደ ጣፋጭ ጒርሻ ነው፤ወደ ሰው ውስጣዊ ክፍል ዘልቆ ይገባል።

9. ለሥራው ደንታ የሌለው ሰው፣የአጥፊ ወንድም ነው።

10. የእግዚአብሔር ስም ጽኑ ግንብ ነው፤ጻድቅ ወደ እርሱ በመሮጥ ተገን ያገኝበታል።

11. የባለጠጎች ሀብት የተመሸገ ከተማቸው ነው፤እንደማይወጣ ረጅም ግንብም ይቈጥሩታል።

12. ከውድቀቱ በፊት ሰው ልቡ ይታበያል፤ትሕትና ግን ክብርን ትቀድማለች።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 18