ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 18:18-21 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

18. ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።

19. የተበደለ ወንድም ከተመሸገ ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤ጠቡም እንደ ጠንካራ የግንብ መዝጊያ ነው።

20. ሰው በአንደበቱ ፍሬ ሆዱ ይጠግባል፤በከንፈሩም ምርት ይረካል።

21. አንደበት የሞትና የሕይወት ኀይል አላት፤የሚወዷትም ፍሬዋን ይበላሉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 18