ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 18:15-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

15. የአስተዋይ ልብ ዕውቀትን ይገበያል፤የጠቢብም ጆሮ አጥብቆ ይሻታል።

16. እጅ መንሻ ለሰጪው መንገድ ትከፍትለታለች፤ታላላቅ ሰዎች ፊትም ታቀርበዋለች።

17. አስቀድሞ ጒዳዩን የሚያሰማ ትክክለኛ ይመስላል፤ይኸውም ባላንጣው መጥቶ እስከሚመረመር ድረስ ነው።

18. ዕጣ መጣጣል ሙግትን ያስቆማል፤ኀይለኛ ባላንጣዎችንም ይገላግላል።

19. የተበደለ ወንድም ከተመሸገ ከተማ ይበልጥ የማይበገር ነው፤ጠቡም እንደ ጠንካራ የግንብ መዝጊያ ነው።

20. ሰው በአንደበቱ ፍሬ ሆዱ ይጠግባል፤በከንፈሩም ምርት ይረካል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 18