ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 18:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ወዳጅነትን የማይፈልግ ሰው የራሱን ፍላጎት ብቻ ይከተላል፤ቅን የሆነውን ፍርድ ሁሉ ይቃወማል።

2. ተላላ ከማስተዋል ርካታን አያገኝም፤የራሱን ሐሳብ በመግለጥ ግን ደስ ይለዋል።

3. ክፋት ስትመጣ ንቀት ትከተላለች፤ከዕፍረትም ጋር ውርደት ትመጣለች።

4. ከሰው አፍ የሚወጡ ቃላት ጥልቅ ውሆች ናቸው፤የጥበብም ምንጭ እንደሚንዶለዶል ፏፏቴ ነው።

5. ለክፉ ሰው ማድላት፣ንጹሑንም ፍትሕ መንሣት ተገቢ አይደለም።

6. የተላላ ከንፈር ጠብ ያመጣበታል፤አፉም በትር ይጋብዛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 18