ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 17:23-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. ክፉ ሰው ፍትሕ ለማዛባት፣በስውር ጒቦ ይቀበላል።

24. አስተዋይ ሰው ጥበብን ከፊቱ አይለያትም፤የተላሎች ዐይኖች ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታሉ።

25. ተላላ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤ለወለደችውም ምሬት ይሆንባታል።

26. ንጹሑን ሰው መቅጣት ተገቢ አይደለም፤ሹሞችን ስለ ቅንነታቸው መግረፍ መልካም አይደለም።

27. ዐዋቂ ሰው ንግግሩ ቊጥብ ነው፤አስተዋይም መንፈሱ የረጋ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 17