ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 17:20-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

20. ጠማማ ልብ ያለው ሰው አይሳካለትም፤በአንደበቱ የሚቀላምድም መከራ ላይ ይወድቃል።

21. ተላላ ልጅ መውለድ ሐዘን ያስከትላል፤የተላላም አባት ደስታ የለውም።

22. ደስተኛ ልብ ጥሩ መድኀኒት ነው፤የተሰበረ መንፈስ ግን ዐጥንትን ያደርቃል።

23. ክፉ ሰው ፍትሕ ለማዛባት፣በስውር ጒቦ ይቀበላል።

24. አስተዋይ ሰው ጥበብን ከፊቱ አይለያትም፤የተላሎች ዐይኖች ግን እስከ ምድር ዳርቻ ይንከራተታሉ።

25. ተላላ ልጅ በአባቱ ላይ ሐዘን ያስከትላል፤ለወለደችውም ምሬት ይሆንባታል።

26. ንጹሑን ሰው መቅጣት ተገቢ አይደለም፤ሹሞችን ስለ ቅንነታቸው መግረፍ መልካም አይደለም።

27. ዐዋቂ ሰው ንግግሩ ቊጥብ ነው፤አስተዋይም መንፈሱ የረጋ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 17