ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 17:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ጠብ እያለ ግብዣፈ ከሞላበት ቤት ይልቅ፣በሰላምና በጸጥታ የእንጀራ ድርቆሽ ይሻላል።

2. ጠቢብ አገልጋይ በወራዳ ልጅ ላይ ሥልጣን ይኖረዋል፤ከወንድማማቾቹም እንደ አንዱ ውርስ ይካፈላል።

3. ማቅለጫ ለብር፣ ከውር ለወርቅ ነው፤ እግዚአብሔር ግን ልብን ይመረምራል።

4. እኵይ ሰው ክፉ ንግግር ያዳምጣል፤ሐሰተኛም የተንኰለኛን አንደበት በጥንቃቄ ይሰማል።

5. በድኾች የሚያፌዝ ፈጣሪያቸውን ይንቃል፤በሌላው ሰው መከራ ደስ የሚለው ከቅጣት አያመልጥም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 17