ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 15:26-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

26. እግዚአብሔር የክፉውን ሰው ሐሳብ ይጸየፋል፤የንጹሓን ሐሳብ ግን ደስ ያሰኘዋል።

27. ስስታም ሰው በቤተ ሰቡ ላይ ችግር ያመጣል፤ጒቦን የሚጠላ ግን በሕይወት ይኖራል።

28. የጻድቅ ሰው ልብ የሚሰጠውን መልስ ያመዛዝናል፤የክፉ ሰው አፍ ግን ክፋትን ያጐርፋል።

29. እግዚአብሔር ከክፉዎች ሩቅ ነው፤የጻድቃንን ጸሎት ግን ይሰማል።

30. ብሩህ ገጽታ ልብን ደስ ያሰኛል፤መልካም ዜናም ዐጥንትን ያለመልማል።

31. ሕይወት ሰጪ የሆነውን ተግሣጽ የሚሰማ፣በጠቢባን መካከል ይኖራል።

32. ተግሣጽን የሚንቅ ራሱን ይንቃል፤ዕርምትን የሚቀበል ግን ማስተዋልን ያገኛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 15