ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 12:23-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

23. አስተዋይ ሰው ዕውቀቱን ይሰውራል፤የተላሎች ልብ ግን ድንቍርናን ይነዛል።

24. ትጉ እጆች ለገዥነት ሲያበቁ፣የስንፍና ፍጻሜ ግን የባርነት ሥራ ነው።

25. ሥጉ ልብ ሰውን በሐዘን ይወጥራል፤መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።

26. ጻድቅ ሰው ለወዳጁ መልካም ምክር ይሰጣል፤የክፉዎች መንገድ ግን ወደ ስሕተት ይመራቸዋል።

27. ሰነፍ አድኖ ያመጣውን እንኳ አይጠብስም፤ትጉ ሰው ግን ለንብረቱ ዋጋ ይሰጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 12