ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 12:16-27 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

16. ተላላ ሰው ቊጣው ወዲያውኑ ይታወቅበታል፤አስተዋይ ሰው ግን ስድብን ንቆ ይተዋል።

17. ሐቀኛ ምስክር በእውነት ይመሰክራል፤ሐሰተኛ ምስክር ግን ውሸት ይናገራል።

18. ግድ የለሽ ቃል እንደ ሰይፍ ይወጋል፤የጠቢብ አንደበት ግን ፈውስን ያመጣል።

19. እውነት የሚናገሩ ከንፈሮች ለዘላለም ጸንተው ይኖራሉ፤ሐሰተኛ አንደበት ግን ለቅጽበት ያህል ብቻ ነው።

20. ክፋትን በሚያውጠነጥኑ ሰዎች ልብ አታላይነት አለ፤ሰላምን የሚያራምዱ ግን ደስታ አላቸው።

21. ጻድቃን ጒዳት አያገኛቸውም፤ክፉዎች ግን በመከራ የተሞሉ ናቸው።

22. እግዚአብሔር ሐሰተኛ ከንፈርን ይጸየፋል፤በእውነተኞች ሰዎች ግን ደስ ይለዋል።

23. አስተዋይ ሰው ዕውቀቱን ይሰውራል፤የተላሎች ልብ ግን ድንቍርናን ይነዛል።

24. ትጉ እጆች ለገዥነት ሲያበቁ፣የስንፍና ፍጻሜ ግን የባርነት ሥራ ነው።

25. ሥጉ ልብ ሰውን በሐዘን ይወጥራል፤መልካም ቃል ግን ደስ ያሰኘዋል።

26. ጻድቅ ሰው ለወዳጁ መልካም ምክር ይሰጣል፤የክፉዎች መንገድ ግን ወደ ስሕተት ይመራቸዋል።

27. ሰነፍ አድኖ ያመጣውን እንኳ አይጠብስም፤ትጉ ሰው ግን ለንብረቱ ዋጋ ይሰጣል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 12