ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 1:28-32 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

28. “በዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ነገር ግን አያገኙኝም።

29. ዕውቀትን ስለ ጠሉ፣ እግዚአብሔርንም መፍራት ስላልመረጡ፣

30. ምክሬን ለመቀበል ስላልፈለጉ፣ዘለፋዬን ስለናቁ፣

31. የመንገዳቸውን ፍሬ ይበላሉ፤የዕቅዳቸውንም ውጤት ይጠግባሉ።

32. ብስለት የሌላቸውን ስድነታቸው ይገድላቸዋል፤ተላሎችንም ቸልተኝነታቸው ያጠፋቸዋል፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 1