ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 1:24-29 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

24. ነገር ግን በተጣራሁ ጊዜ እምቢ ስላላችሁኝ፣እጄንም ስዘረጋ ማንም ግድ ስላልነበረው፣

25. ምክሬን ሁሉ ስለናቃችሁ፣ዘለፋዬንም ስላልተቀበላችሁ፣

26. እኔ ደግሞ በመከራችሁ እሥቅባችኋለሁ፤መዓት በሚወርድባችሁም ጊዜ አፌዝባችኋለሁ፤

27. መዓት እንደ ማዕበል ሲያናውጣችሁ፣መከራም እንደ ዐውሎ ነፋስ ሲጠራርጋችሁ፣ሥቃይና ችግር ሲያጥለቀልቃችሁ አፌዝባችኋለሁ።

28. “በዚያን ጊዜ ይጠሩኛል፤ እኔ ግን አልመልስላቸውም፤አጥብቀው ይፈልጉኛል፤ ነገር ግን አያገኙኝም።

29. ዕውቀትን ስለ ጠሉ፣ እግዚአብሔርንም መፍራት ስላልመረጡ፣

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 1