ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ምሳሌ 1:1-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. የእስራኤል ንጉሥ፣ የዳዊት ልጅ የሰሎሞን ምሳሌዎች፤

2. ጥበብንና ተግሣጽን ለመቀበል፤ጥልቅ ሐሳብ የሚገልጡ ቃላትን ለማስተዋል፤

3. ጽድቅን፣ ፍትሕንና ሚዛናዊ ብያኔን በማድረግ፣የተገራ ጠቢብ ልቦናን ለማግኘት፤

4. ብስለት ለሌላቸው አስተዋይነትን፣በዕድሜ ለጋ ለሆኑት ዕውቀትንና ልባምነትን ለመስጠት፤

5. ጥበበኞች ያድምጡ፤ ትምህርታቸውንም ያዳብሩ፤አስተዋዮችም መመሪያ ያግኙበት፤

6. ይህም የጠቢባንን ምሳሌዎችንና ተምሳሌቶችን፣አባባሎችንና ዕንቆቅልሾችን ይረዱ ዘንድ ነው።

7. እግዚአብሔርን መፍራት የዕውቀት መጀመሪያ ነው፤ተላሎች ግን ጥበብንና ተግሣጽን ይንቃሉ።

8. ልጄ ሆይ፤ የአባትህን ምክር አድምጥ፤የእናትህንም ትምህርት አትተው።

9. ለራስህ ሞገስን የሚያጐናጽፍ አክሊል፣ዐንገትህን የሚያስውብ ድሪ ይሆንልሃል።

10. ልጄ ሆይ፤ ኀጢአተኞች ቢያባብሉህ፣እሺ አትበላቸው፤

11. “ከእኛ ጋር ናና፣ ደም ለማፍሰስ እናድባ፤በደል በሌለበት ሰው ላይ እንሸምቅ፤

12. እንደ መቃብር፣ ወደ ጒድጓድ እንደሚወርዱ፣ከነሕይወታቸው እንዳሉ እንዋጣቸው፤

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ምሳሌ 1