ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 8:1-5 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ምነው አንተ የእናቴን ጡት እንደ ጠባ፣እንደ ወንድሜ በሆንህ!ከዚያም ውጭ ባገኝህ፣እስምህ ነበር፤ታዲያ ማንም ባልናቀኝ!

2. እኔም ወደ አስተማረችኝ፣ወደ እናቴም ቤት፣እጅህን ይዤ በወሰድሁህ ነበር፤የምትጠጣውን ጣፋጭ የወይን ጠጅ፣የሮማኔን ጭማቂም በሰጠሁህ።

3. ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ቀኝ እጁም ዐቅፎኛል።

4. እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፤ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት እማጠናችኋለሁ።

5. ውዷን ተደግፋ፣ከምድረ በዳ የምትወጣ ይህች ማን ናት?ከእንኰይ ዛፍ ሥር አስነሣሁህ፤ በዚያ እናትህ ፀነሰችህ፤በዚያም ታምጥ የነበረችው አንተንወለደችህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 8