ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 7:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ከናፍሮችሽም እንደ ማለፊያ የወይን ጠጅ ይጣፍጡ።የወይን ጠጁ በቀስታ እየተንቈረቈረ፣ወደ ውዴ ከንፈሮችና ጥርሶች ይውረድ።

10. እኔ የውዴ ነኝ፤የእርሱም ምኞት እኔው ነኝ።

11. ውዴ ሆይ፤ ና ወደ ገጠር እንሂድ፤ወደ መንደርም ገብተን እንደር፤

12. ማልደን ወደ ወይኑ ተክል ቦታ እንሂድ፣ወይኑ እንቡጥ አውጥቶ፣አበባው ፈክቶ፣ሮማኑ አፍርቶ እንደሆነ እንይ፤በዚያም ራሴን በፍቅር እሰጥሃለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 7