ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 6:6-10 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ጥርሶችሽከመታጠቢያ እንደ ወጡ የበግ መንጋ ናቸው፤ሁሉም መንታ መንታ የወለዱ፣ከመካከላቸውም መካን የሌለባቸው ናቸው።

7. ከመሸፈኛሽ ውስጥ ያሉት ጒንጮችሽ፣ለሁለት የተከፈለ ሮማን ይመስላሉ።

8. ሥልሳ ንግሥቶች፣ሰማንያ ቁባቶች፣ቊጥራቸውም የበዛ ደናግል ሊኖሩ ይችላሉ፤

9. እንከን የሌለባት ርግቤ ግን ልዩ ናት፤እርሷ ለወለደቻት የተመረጠች፤ለእናቷም አንዲት ናት፤ቈነጃጅት አይተው “የተባረክሽ ነሽ”አሏት፤ንግሥቶችና ቁባቶችም አመሰገኗት።

10. እንደ ንጋት ብርሃን ብቅ የምትል፣እንደ ጨረቃ የደመቀች፣ እንደ ፀሓይ ያበራች፣ዐርማ ይዞ በሰልፍ እንደ ወጣ ሰራዊት ግርማዋ የሚያስፈራ ይህች ማን ናት?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 6