ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 5:10-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

10. ውዴ ፍልቅልቅና ደመ ግቡ ነው፤ከዐሥር ሺሆችም የሚልቅ ነው።

11. ራሱ የጠራ ወርቅ፣ጠጒሩ ዞማ፣እንደ ቊራም የጠቈረ ነው።

12. ዐይኖቹ፣በጅረት አጠገብ እንዳሉ ርግቦች፣በወተት የታጠቡ፣እንደ ዕንቊም ጒብ ጒብ ያሉ ናቸው።

13. ጒንጮቹ የሽቱ መዐዛ የሚያመጡ፣የቅመማ ቅመም መደቦችን ይመስላሉ፤ከንፈሮቹም ከርቤ እንደሚያንጠባጥቡ፣ውብ አበቦች ናቸው።

14. ክንዶቹ በዕንቊ ፈርጥ ያጌጠ፣የወርቅ ዘንግን ይመስላሉ፤ሰውነቱም በሰንፔር ፈርጥ ያጌጠ፣አምሮ የተሠራ የዝሆን ጥርስን ይመስላል።

15. እግሮቹ በንጹሕ ወርቅ መቆሚያ ላይ የተተከሉ፣የዕብነ በረድ ምሰሶዎችን ይመስላሉ፤መልኩ እንደ ሊባኖስ ነው፤እንደ ዝግባ ዛፎቹም ምርጥ ነው።

16. አፉ ራሱ ጣፋጭ ነው፤ሁለንተናውም ያማረ ነው፤እናንተ የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤ውዴ ይህ ነው፤ ባልንጀራዬም እርሱ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 5