ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 2:9-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ውዴ ሚዳቋ ወይም የዋልያ ግልገል ይመስላል፤እነሆ፤ ከቤታችን ግድግዳ ኋላ ቆሞአል፤በመስኮት ትክ ብሎ ወደ ውስጥ ያያል፤በፍርግርጉም እያሾለከ ይመለከታል።

10. ውዴም እንዲህ አለኝ፤“ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺ፤አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋር ነዪ።

11. እነሆ! ክረምቱ ዐለፈ፤ዝናሙም አባርቶ አበቃ፤

12. አበቦች በምድር ላይ ታዩ፤የዝማሬ ወቅት መጥቶአል፤የርግቦችም ድምፅ፣በምድራችን ተሰማ።

13. በለስ ፍሬዋን አፈራች፤ያበቡ ወይኖችም መዐዛቸውን ሰጡ፤ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺና ነዪ፤አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋር ነዪ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 2