ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 2:7-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት፣ራሱ እስኪፈልግ ድረስ፣ፍቅርን እንዳታስነሡት ወይም እንዳትቀሰቅሱት፣በሚዳቋና በሜዳ ዋልያ አማጥናችኋለሁ።

8. እነሆ፤ የውዴ ድምፅበተራሮች ላይ እየዘለለ፣በኰረብቶችም ላይ እየተወረወረ፣ሲመጣ ይሰማኛል።

9. ውዴ ሚዳቋ ወይም የዋልያ ግልገል ይመስላል፤እነሆ፤ ከቤታችን ግድግዳ ኋላ ቆሞአል፤በመስኮት ትክ ብሎ ወደ ውስጥ ያያል፤በፍርግርጉም እያሾለከ ይመለከታል።

10. ውዴም እንዲህ አለኝ፤“ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺ፤አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋር ነዪ።

11. እነሆ! ክረምቱ ዐለፈ፤ዝናሙም አባርቶ አበቃ፤

12. አበቦች በምድር ላይ ታዩ፤የዝማሬ ወቅት መጥቶአል፤የርግቦችም ድምፅ፣በምድራችን ተሰማ።

13. በለስ ፍሬዋን አፈራች፤ያበቡ ወይኖችም መዐዛቸውን ሰጡ፤ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺና ነዪ፤አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋር ነዪ።”

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 2