ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 2:11-16 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

11. እነሆ! ክረምቱ ዐለፈ፤ዝናሙም አባርቶ አበቃ፤

12. አበቦች በምድር ላይ ታዩ፤የዝማሬ ወቅት መጥቶአል፤የርግቦችም ድምፅ፣በምድራችን ተሰማ።

13. በለስ ፍሬዋን አፈራች፤ያበቡ ወይኖችም መዐዛቸውን ሰጡ፤ፍቅሬ ሆይ፤ ተነሺና ነዪ፤አንቺ የእኔ ቈንጆ፤ ከእኔ ጋር ነዪ።”

14. አንቺ በገደል ዐለት ንቃቃት፣በተራሮችም ባሉ መደበቂያ ስፍራዎች ውስጥ ያለሽ ርግቤ ሆይ!ፊትሽን አሳይኝ፤ድምፅሽንም አሰሚኝ፤ድምፅሽ ጣፋጭ፣መልክሽም ውብ ነውና።

15. የወይን ተክሉን ቦታ፣በማበብ ላይ ያለውን የወይን ተክል ቦታችንን፣የሚያጠፉትን ቀበሮዎች፣እነዚያን ትንንሽ ቀበሮዎች አጥምዳችሁ ያዙልን።

16. ውዴ የእኔ ነው፤ እኔም የእርሱ ነኝ፣እርሱ መንጋውን በውብ አበቦች መካከል ያሰማራል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 2