ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 2:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እኔ የሳሮን ጽጌረዳ፣የሸለቆም አበባ ነኝ።

2. በእሾኽ መካከል እንዳለ ውብ አበባ፣ውዴም በቈነጃጅት መካከል እንዲሁ ናት።

3. በዱር ዛፎች መካከል እንዳለ እንኰይ፣ውዴም በጐልማሶች መካከል እንዲሁ ነው፤በጥላው ሥር መቀመጥ ደስ ያሰኛል፤የፍሬውም ጣፋጭነት ያረካኛል።

4. ወደ ግብዣው አዳራሽ ወሰደኝ፤በእኔ ላይ ያለው ዐላማው ፍቅር ነው።

5. በዘቢብ አበረታቱኝ፤በእንኰይም አስደስቱኝ፤በፍቅሩ ተይዤ ታምሜአለሁና።

6. ግራ እጁን ተንተርሻለሁ፤ቀኝ እጁም ዐቅፎኛል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 2