ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 1:4-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

4. ይዘኸኝ ሂድ፤ እንፍጠን፤ንጉሡ ወደ ዕልፍኞቹ አምጥቶኛል።በአንተ ደስ ይለናል፤ ሐሤትም እናደርጋለን፤ከወይን ጠጅ ይልቅ ፍቅርህን እንወድሳለን።አንተን እንደዚህ ማፍቀራቸው ትክክል ነው።

5. እናንት የኢየሩሳሌም ቈነጃጅት ሆይ፤እኔ ጥቊር ነኝ፤ ይሁን እንጂ ውብ ነኝ፤ጥቊረቴ እንደ ቄዳር ድንኳኖች፣እንደ ሰሎሞን ቤተ መንግሥት መጋረጃዎችም ነው።

6. ጥቊር ስለ ሆንሁ ትኵር ብላችሁ አትዩኝ፤መልኬን ያጠቈረው ፀሓይ ነውና፤የእናቴ ልጆች ወንድሞቼ ተቈጡኝ፤የወይን ተክል ቦታዎችም ጠባቂ አደረጉኝ፤የራሴን የወይን ተክል ቦታ ተውሁት።

7. ውዴ ሆይ፤ መንጋህን የት እንደምታሰማራ፣በቀትርም የት እንደምትመስጋቸውእባክህ ንገረኝ፤በወዳጆችህ መንጎች ኋላ፣ፊቷን ሸፍና እንደምትቅበዘበዝ ሴት ለምን ልሁን?

8. አንቺ ከሴቶች ሁሉ ይበልጥ የተዋብሽ ሆይ፤ የማታውቂ ከሆነ፣የበጎቹን ዱካ ተከተዪ፤የፍየል ግልገሎችሽንም፣በእረኞቹ ድንኳን አጠገብ አሰማሪ።

9. ውዴ ሆይ፤ የፈርዖንን ሠረገሎች ከሚስቡ ፈረሶች መካከል፣በአንዲቱ ባዝራ መሰልሁሽ።

10. ጒንጮችሽ በጒትቻ፣ዐንገትሽም በዕንቊ ሐብል አጊጠዋል።

11. እኛም ባለ ብር ፈርጥ፣የወርቅ ጒትቻ እናሠራልሻለን።

12. ንጉሡ ማእዱ ላይ ሳለ፣ሽቱዬ መዐዛውን ናኘው።

13. ውዴ ለእኔ በጡቶቼ መካከል እንዳረፈ፣በመቋጠሪያ እንዳለ ከርቤ ነው።

14. ውዴ ለእኔ ከዓይንጋዲ የወይን ተክል ቦታ፣እንደ መጣ የሄና አበባ ዕቅፍ ነው።

15. ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽእንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽዐይኖችሽም እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው።

16. አንተ ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነህእንዴትስ ታምራለህዐልጋችንም እንደ ለምለም ሣር ነው።

17. የቤታችን ተሻካሚዎች ዝግባዎች፣የጣራችን ማዋቀሪያዎችም ጥዶች ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 1