ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ማሕልየ መሓልይ 1:12-17 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

12. ንጉሡ ማእዱ ላይ ሳለ፣ሽቱዬ መዐዛውን ናኘው።

13. ውዴ ለእኔ በጡቶቼ መካከል እንዳረፈ፣በመቋጠሪያ እንዳለ ከርቤ ነው።

14. ውዴ ለእኔ ከዓይንጋዲ የወይን ተክል ቦታ፣እንደ መጣ የሄና አበባ ዕቅፍ ነው።

15. ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነሽእንዴትስ ያለሽ ቈንጆ ነሽዐይኖችሽም እንደ ርግብ ዐይኖች ናቸው።

16. አንተ ውዴ ሆይ፤ እንዴት ውብ ነህእንዴትስ ታምራለህዐልጋችንም እንደ ለምለም ሣር ነው።

17. የቤታችን ተሻካሚዎች ዝግባዎች፣የጣራችን ማዋቀሪያዎችም ጥዶች ናቸው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ማሕልየ መሓልይ 1