ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 6:7-14 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. በአንድ ሺህ አውራ በጎች፣በዐሥር ሺህ የዘይት ፈሳሽ እግዚአብሔር ደስ ይለዋልን?ስለ በደሌ የበኵር ልጄን፣ስለ ነፍሴም ኀጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብለትን?

8. ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?

9. ስምህን መፍራት ጥበብ ነው፤ስሙ! እግዚአብሔር ከተማዪቱን እንዲህ እያለ ይጣራል፤“በትሩን አስቡ፤ ያዘጋጀውም ማን እንደሆነ አስታውሱ።

10. የክፋት ቤት ሆይ፤በግፍ የተገኘ ሀብታችሁን፣በሐሰተኛ መስፈሪያ የሰበሰባችሁትን አስጸያፊ ነገር እረሳዋለሁን?

11. አባይ ሚዛን የያዘውን ሰው፣ሐሰተኛ መመዘኛ በከረጢት የቋጠረውን ንጹሕ ላድርገውን?

12. ባለጠጎቿ ግፈኞች፣ሰዎችዋ ሐሰተኞች ናቸው፤ምላሳቸውም አታላይ ናት።

13. ስለዚህ አንተን አጠፋሃለሁ፣ከኀጢአትህ የተነሣ አፈራርስሃለሁ።

14. ትበላለህ፤ ነገር ግን አትጠግብም፤ሆድህ እንዳለ ባዶውን ይቀራል፤ታከማቻለህ፤ ነገር ግን አይጠራቀምልህም፤የሰበሰብኸውን ለሰይፍ አደርገዋለሁና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 6