ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 6:3-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. “ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ?ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው?እስቲ መልስልኝ!

4. ከግብፅ አወጣሁህ፤ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤እንዲመሩህ ሙሴን፣አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።

5. ሕዝቤ ሆይ፤የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፣የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትንም እስቲ አስቡ፤ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ታውቁ ዘንድ፣ከሰጢም እስከ ጌልገላ የተጓዛችሁትን አስቡ።

6. ምን ይዤበእግዚአብሔር ፊት ልቅረብ፣በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ?የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ከአንድ ዓመት ጥጃ ጋር ይዤ በፊቱ ልቅረብን?

7. በአንድ ሺህ አውራ በጎች፣በዐሥር ሺህ የዘይት ፈሳሽ እግዚአብሔር ደስ ይለዋልን?ስለ በደሌ የበኵር ልጄን፣ስለ ነፍሴም ኀጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብለትን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 6