ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 6:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር የሚለውን ስሙ፤“ተነሡ፤ ጒዳያችሁን በተራሮችም፤ፊት አቅርቡ፤ኰረብቶች እናንተ የምትሉትን ይስሙ፤

2. ተራሮች ሆይ፤ የእግዚአብሔርን ክስ አድምጡ፤እናንት የምድር ጽኑ መሠረቶችም፤ ስሙ፤ እግዚአብሔር ከሕዝቡ ጋር ክርክር አለውና፤ከእስራኤልም ጋር ይፋረዳል።

3. “ሕዝቤ ሆይ፤ ምን አድርጌሃለሁ?ሸክም የሆንሁብህስ እንዴት ነው?እስቲ መልስልኝ!

4. ከግብፅ አወጣሁህ፤ከባርነት ምድርም ተቤዠሁህ፤እንዲመሩህ ሙሴን፣አሮንንና ማርያምን ላክሁልህ።

5. ሕዝቤ ሆይ፤የሞዓብ ንጉሥ ባላቅ የመከረውን፣የቢዖር ልጅ በለዓም የመለሰለትንም እስቲ አስቡ፤ የእግዚአብሔርን የጽድቅ ሥራ ታውቁ ዘንድ፣ከሰጢም እስከ ጌልገላ የተጓዛችሁትን አስቡ።

6. ምን ይዤበእግዚአብሔር ፊት ልቅረብ፣በልዑል አምላክ ፊት ልስገድ?የሚቃጠለውን መሥዋዕት፣ከአንድ ዓመት ጥጃ ጋር ይዤ በፊቱ ልቅረብን?

7. በአንድ ሺህ አውራ በጎች፣በዐሥር ሺህ የዘይት ፈሳሽ እግዚአብሔር ደስ ይለዋልን?ስለ በደሌ የበኵር ልጄን፣ስለ ነፍሴም ኀጢአት የሆዴን ፍሬ ላቅርብለትን?

8. ሰው ሆይ፤ መልካም የሆነውን አሳይቶሃል፤ እግዚአብሔር ከአንተ የሚፈልገው ምንድን ነው?ፍትሕን ታደርግ ዘንድ፣ ምሕረትንም ትወድድ ዘንድ፣በአምላክህም ፊት በትሕትና ትራመድ ዘንድ አይደለምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 6