ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 2:6-13 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ።

7. የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እንዲህ ሊባል ይገባልን?“የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን?እንዲህ ያሉት ነገሮችንስ ያደርጋልን?”“መንገዱ ቀና ለሆነ፣ቃሌ መልካም አያደርግምን?

8. በመጨረሻ በሕዝቤ ላይ ጠላት ሆናችሁተነሣችሁ፤የጦርነት ሐሳብ ሳይኖራቸው፣በሰላም ከሚያልፉ ሰዎች ላይ፣ማለፊያ መጐናጸፊያ ገፈፋችሁ።

9. ከሚወዱት ቤታቸው፣የሕዝቤን ሴቶች አስወጣችኋቸው፤ክብሬን ከልጆቻቸው፣ለዘላለም ወሰዳችሁ።

10. ተነሡና፤ ከዚያ ሂዱ፤ይህ ማረፊያ ቦታችሁ አይደለምና፤ምክንያቱም ረክሶአል፤ክፉኛም ተበላሽቶአል።

11. ሐሰተኛና አታላይ ሰው መጥቶ፣‘ስለ ብዙ የወይን ጠጅና ስለሚያሰክር መጠጥ ትንቢት እነግራችኋለሁ’ ቢል፣ለዚህ ሕዝብ ተቀባይነት ያለው ነቢይ ይሆናል።

12. “ያዕቆብ ሆይ፤ በእርግጥ ሁላችሁንም እሰበስባለሁ፤የእስራኤልንም ትሩፍ በአንድነት አመጣለሁ፤በጒረኖ ውስጥ እንዳሉ በጎች በመሰማሪያ ላይ እንዳለ መንጋ በአንድነትእሰበስባቸዋለሁ፤ቦታውም በሕዝብ ይሞላል።

13. የሚሰብረው ወጥቶ በፊታቸው ይሄዳል፤እነርሱም በሩን በመስበር ወጥተው ይሄዳሉ፤ እግዚአብሔር እየመራቸው፣ንጉሣቸው ቀድሞአቸው ይሄዳል።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 2