ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 2:1-7 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው!ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።

2. ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤የሰውን ቤት፣የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።

3. ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ከዚህም ለማምለጥ አትችሉም።ከእንግዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤የመከራ ጊዜ ይሆናልና።

4. በዚያ ቀን ሰዎች ይሣለቁባችኋል፤በሐዘን እንጒርጒሮ እንዲህ እያሉ ያፌዙባችኋል፤‘እኛ ፈጽሞ ጠፍተናል፤የወገኔ ርስት ተከፋፍሎአል።ከእኔ ነጥቆ ወስዶ፣ዕርሻዎቻችንን ላሸነፉን አከፋፈለ።’

5. ስለዚህ በእግዚአብሔር ጉባኤ ውስጥ፣መሬት በዕጣ የሚያካፍል ማንም አይኖርም።

6. ነቢያቶቻቸው፣ “ትንቢት አትናገርብን፤ስለ እነዚህ ነገሮች ትንቢት አትናገር፤ውርደት አይደርስብንም” ይላሉ።

7. የያዕቆብ ቤት ሆይ፤ እንዲህ ሊባል ይገባልን?“የእግዚአብሔር መንፈስ የማይታገሥ ነውን?እንዲህ ያሉት ነገሮችንስ ያደርጋልን?”“መንገዱ ቀና ለሆነ፣ቃሌ መልካም አያደርግምን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 2