ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 2:1-3 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. ክፉ ለመሥራት ለሚያቅዱ፣በመኝታቸው ሳሉ ተንኰል ለሚያውጠነጥኑ ወዮላቸው!ሲነጋ በማለዳ ይፈጽሙታል፤የሚያደርጉበት ኀይል በእጃቸው ነውና።

2. ዕርሻ ይመኛሉ፤ ይይዙታልም፤ቤት ይመኛሉ፤ ይወስዱታልም፤የሰውን ቤት፣የባልንጀራን ርስት አታልለው ይወስዳሉ።

3. ስለዚህ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል፤“እነሆ፤ በዚያ ሕዝብ ላይ ጥፋት ላመጣ ዐቅጃለሁ፤ከዚህም ለማምለጥ አትችሉም።ከእንግዲህ በትዕቢት አትመላለሱም፤የመከራ ጊዜ ይሆናልና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 2