ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 1:7-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. ጣዖቶችዋ ሁሉ ይሰባበራሉ፤ለቤተ መቅደሷ የቀረበው ገጸ በረከት በእሳት ይቃጠላል፤ምስሎችዋን ሁሉ እደመስሳለሁ፤ገጸ በረከቷን በዝሙት አዳሪነት እንደ ሰበሰበች ሁሉ፣አሁንም ገጸ በረከትዋ የዝሙት አዳሪነት ዋጋ መቀበያ ይሆናል።

8. በዚህ ምክንያት አለቅሳለሁ፤ ዋይ ዋይም እላለሁ፤ባዶ እግሬንና ዕርቃኔን እሄዳለሁ፤እንደ ቀበሮ አላዝናለሁ፤እንደ ጒጒትም አቃስታለሁ።

9. ቊስሏ የማይሽር ነውና፤ለይሁዳ ተርፎአል፤እስከ ሕዝቤ መግቢያ በር፣እስከ ኢየሩሳሌም እንኳ ደርሶአል።

10. በጌት አታውሩት፤ከቶም አታልቅሱ፤በቤትዓፍራ፣በትቢያ ላይ ተንከባለሉ።

11. እናንት በሻፊር የምትኖሩ፣ዕርቃናችሁን ሆናችሁ በኀፍረት ዕለፉ፤በጸዓናን የሚኖሩከዚያ አይወጡም፤ቤትዔጼል በሐዘን ላይ ናት፤ለእናንተም መጠጊያ ልትሆን አትችልም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 1