ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚክያስ 1:1-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. በይሁዳ ነገሥታት በኢዮአታም፣ በአካዝና በሕዝቅያስ ዘመን ወደ ሞሬታዊው ወደ ሚክያስ የመጣው የእግዚአብሔር ቃል፣ ስለ ሰማርያና ስለ ኢየሩሳሌም ያየው ራእይ ይህ ነው፤

2. እናንተ አሕዛብ ሆይ፤ ሁላችሁም ስሙ፤ምድር ሆይ፤ በውስጧም የምትኖሩ ሁሉ አድምጡ፤ጌታ ከቅዱስ መቅደሱ፣ልዑል እግዚአብሔር በእናንተ ላይ ይመሰክርባችኋል።

3. እነሆ፤ እግዚአብሔር ከመኖሪያ ስፍራው ይመጣል፤ወርዶም በምድር ከፍታዎች ላይ ይራመዳል።

4. ተራሮች ከሥሩ ይቀልጣሉ፤ሸለቆዎችም ይሰነጠቃሉ፤በእሳት ፊት እንዳለ ሰም፣በገደል ላይ እንደሚወርድ ፈሳሽ ይሆናሉ።

5. ይህ ሁሉ የሚሆነው ስለ ያዕቆብ በደል፣ስለ እስራኤልም ቤት ኀጢአት ነው።የያዕቆብ በደል ምንድን ነው?ሰማርያ አይደለችምን?የይሁዳስ የኰረብታ መስገጃ ምንድን ነው?ኢየሩሳሌም አይደለችምን?

6. “ስለዚህ ሰማርያን የፍርስራሽ ክምር፣ወይን የሚተከልባትም ስፍራ አደርጋታለሁ፤ድንጋዮቿን ወደ ሸለቆ አወርዳለሁ፤መሠረቷንም ባዶ አደርጋለሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚክያስ 1