ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

ሚልክያስ 1:7-9 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

7. “በመሠዊያዬ ላይ የረከሰ ምግብ ታስቀምጣላችሁ።“እናንተ ግን፣ ‘ያረከስንህ እንዴት ነው?’ አላችሁ።“የእግዚአብሔር ገበታ የተናቀ ነው በማለታችሁ ነው።

8. የታወረውን እንስሳ ለመሥዋዕት ስታቀርቡ፣ ያ በደል አይደለምን? አንካሳውን ወይም በሽተኛውን እንስሳ መሥዋዕት አድርጋችሁ ስታቀርቡ፣ ያስ በደል አይደለምን? ያንኑ ለገዣችሁ ብታቀርቡ፣ በእናንተ ደስ ይለዋልን? ወይስ ይቀበለዋልን?” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

9. “አሁን ግን እንዲራራልን እግዚአብሔርን ለምኑ፤ እንደዚህ ዐይነቱን መሥዋዕት ይዛችሁ ስትቀርቡ ይቀበላችኋልን?” ይላል እግዚአብሔር ጸባኦት።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ ሚልክያስ 1