ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 99:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ነገሠ፤ሕዝቦች ይንቀጥቀጡ፤በኪሩቤል ላይ በዙፋን ተቀምጦአል፤ምድር ትናወጥ።

2. እግዚአብሔር በጽዮን ታላቅ ነው፤ከሕዝቦችም ሁሉ በላይ ከፍ ከፍ ብሎአል።

3. ታላቁንና አስፈሪውን ስምህን ይወድሱ፤እርሱ ቅዱስ ነው።

4. ፍትሕን የምትወድ፣ ኀያል ንጉሥ ሆይ፤አንተ ትክክለኝነትን መሠረትህ፤ፍትሕንና ቅንነትንም፣ለያዕቆብ አደረግህ።

5. አምላካችንን እግዚአብሔርን ከፍ ከፍ አድርጉት፤በእግሩ መርገጫ ስገዱ፤እርሱ ቅዱስ ነውና።

6. ሙሴና አሮን ካህናቱ ከሆኑት መካከል ነበሩ፤ሳሙኤልም ስሙን ከጠሩት መካከል አንዱ ነበረ፤እነርሱ ወደ እግዚአብሔር ተጣሩ፤እርሱም መለሰላቸው።

7. ከደመና ዐምድ ውስጥ ተናገራቸው፤እነርሱም ሥርዐቱንና የሰጣቸውን ድንጋጌ ጠበቁ።

8. እግዚአብሔር አምላካችን ሆይ፤አንተ መለስህላቸው፤ጥፋታቸውን ብትበቀልም እንኳ፣አንተ ይቅር የምትላቸው አምላክ ነህ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 99