ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 97:9-12 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ በምድር ሁሉ ላይ ልዑል ነህና፤ከአማልክትም ሁሉ በላይ እጅግ ከፍ ያልህ ነህ።

10. እግዚአብሔርን የምትወዱ ክፋትን ጥሉ፤እርሱ የታማኞቹን ነፍስ ይጠብቃልና፤ከዐመፀኞችም እጅ ይታደጋቸዋል።

11. ብርሃን ለጻድቃን፣ሐሤትም ልባቸው ለቀና ወጣ።

12. እናንተ ጻድቃን በእግዚአብሔር ደስ ይበላችሁ፤ቅዱስ ስሙንም አመስግኑ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 97