ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 97:1-8 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ነገሠ፤ ምድር ደስ ይበላት፤በሩቅ ያሉ የባሕር ጠረፎች ሐሤት ያድርጉ።

2. ደመናና ጥቅጥቅ ያለ ጭጋግ በዙሪያው አለ፤ጽድቅና ፍትሕ የዙፋኑ መሠረት ናቸው።

3. እሳት በፊቱ ይሄዳል፤በዙሪያው ያሉትንም ጠላቶቹን ይፈጃል።

4. መብረቁ ዓለምን አበራ፤ምድርም አይታ ተንቀጠቀጠች።

5. ተራሮች በእግዚአብሔር ፊት፣በምድርም ሁሉ ጌታ ፊት እንደ ሰም ቀለጡ።

6. ሰማያት ጽድቁን ያውጃሉ፤ሕዝቦችም ሁሉ ክብሩን ያያሉ።

7. ለተቀረጸ ምስል የሚሰግዱ፣በጣዖታትም የሚመኩ ሁሉ ይፈሩ፤እናንተ አማልክት ሁሉ፤ ለእርሱ ስገዱ።

8. እግዚአብሔር ሆይ፤ ስለ ፍርድህ፣ጽዮን ሰምታ ደስ አላት፤የይሁዳም ሴት ልጆች ሐሤት አደረጉ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 97