ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 95:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ኑ፤ እናምልከው፤ እንስገድለትም፤በፈጣሪያችን በእግዚአብሔር ፊት እንንበርከክ፤

7. እርሱ አምላካችን ነውና፤እኛም በእጁ ጥበቃ ሥር ያለን በጎቹ፣የመሰማሪያውም ሕዝብ ነን።ዛሬ ድምፁን ብትሰሙ፣

8. በምድረ በዳ በነበራችሁበት ቀን በማሳህ፣በመሪባም እንዳደረጋችሁት፣ ልባችሁን አታደንድኑ።

9. ሥራዬን ቢያዩም፣አባቶቻችሁ በዚያ ፈተኑኝ፤ ተፈታተኑኝም።

10. ያን ትውልድ አርባ ዓመት ሙሉ ተቈጣሁት፤እኔም፣ “ልቡ የሸፈተ ሕዝብ ነው፤መንገዴንም አላወቀም” አልሁ።

11. ስለዚህ፣ “ፈጽሞ ወደ ዕረፍቴ አይገቡም” ብዬ፣በቍጣዬ ማልሁ።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 95