ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 94:9-20 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

9. ጆሮን የተከለው እርሱ አይሰማምን? ዐይንንስ የሠራ እርሱ አያይምን?

10. ሕዝቦችን በተግሣጽ ወደ መንገድ የሚመልስ፣ዕውቀትንስ ለሰው ልጆች የሚያስተምር አይቀጣምን?

11. እግዚአብሔር የሰው ሐሳብ መና፣ከንቱም እንደሆነ ያውቃል።

12. እግዚአብሔር ሆይ፤ አንተ የምትገሥጸው፣ከሕግህም የምታስተምረው ሰው ምስጉን ነው።

13. ለኀጢአተኞች ጒድጓድ እስኪማስላቸው ድረስ፣እርሱን ከመከራ ታሳርፈዋለህ።

14. እግዚአብሔር ሕዝቡን አይጥልምና፤ርስቱንም አይተውም።

15. ፍርድ ተመልሶ በጽድቅ አሠራር ላይ ይመሠረታል፤ልባቸውም ቀና የሆነ ሁሉ ይከተሉታል።

16. ክፉዎችን የሚቋቋምልኝ ማን ነው?ከክፉ አድራጊዎችስ ጋር የሚሟገትልኝ ማን ነው?

17. እግዚአብሔር ረዳቴ ባይሆን ኖሮ፣ነፍሴ ወደ ዝምታው ዓለም ፈጥና በወረደች ነበር።

18. እኔ፣ “እግሬ አዳለጠኝ” ባልሁ ጊዜ፣ እግዚአብሔር ሆይ፤ ምሕረትህ ደግፎ ያዘኝ።

19. የውስጤ ጭንቀት በበዛ መጠን፣ማጽናናትህ ነፍሴን ደስ አሰኛት።

20. ዐመፃን ሕጋዊ የሚያደርግ፣የጥፋት ዙፋን ከአንተ ጋር ሊያብር ይችላልን?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 94