ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 90:6-11 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

6. ሣሩም ንጋት ላይ አቈጥቍጦ ይለመልማል፤ምሽት ላይ ጠውልጎ ይደርቃል።

7. በቊጣህ አልቀናልና፤በመዓትህም ደንግጠናል።

8. በደላችንን በፊትህ፣የተሰወረ ኀጢአታችንንም በገጽህ ብርሃን ፊት አኖርህ።

9. ዘመናችን ሁሉ በቊጣህ ዐልፎአልና፤ዕድሜአችንንም በመቃተት እንጨርሳለን።

10. የዕድሜአችን ዘመን ሰባ ዓመት፣ ቢበዛም ሰማንያ ነው፤ከዚያ በላይ ከሆነም ድካምና መከራ ብቻ ነው፤ቶሎ ያልፋልና፤ እኛም ወዲያው እንነጒዳለን።

11. የቍጣህን ኀይል ማን ያውቃል?መዓትህም የመፈራትህን ያህል ታላቅ ነው።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 90