ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 90:1-4 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

1. እግዚአብሔር ሆይ፤አንተ ከትውልድ እስከ ትውልድ መጠጊያችን ሆንህልን።

2. ገና ተራሮች ሳይወለዱ፣ምድርንና ዓለምን ከመፍጠርህ በፊት፣አንተ ከዘላለም እስከ ዘላለም አምላክ ነህ።

3. ሰዎችን ወደ ዐፈር ትመልሳለህ፤“የሰው ልጆች ሆይ፤ ወደ ቦታችሁ ተመለሱ” ትላለህ፤

4. ሺህ ዓመት በፊትህ፣እንዳለፈችው እንደ ትናንት ቀን፣እንደ ሌሊትም እርቦ ነውና።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 90