ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 9:8-18 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

8. ዓለምን በጽድቅ ይዳኛል፤ሕዝቦችንም በፍትሕ ይገዛል።

9. እግዚአብሔር ለተጨቈኑት ዐምባ ነው፤በመከራም ጊዜ መጠጊያ ይሆናቸዋል።

10. ስምህን የሚያውቁ ይታመኑብሃል፤ እግዚአብሔር ሆይ፤ የሚሹህን አትተዋቸውምና።

11. በጽዮን ለሚኖር ለእግዚአብሔር ዘምሩ፤ሥራውንም በሕዝቦች መካከል በግልጽ አውሩ፤

12. ደም ተበቃዩ ዐስቦአቸዋልና፤የጭቍኖችንም ጩኸት አልዘነጋም።

13. እግዚአብሔር ሆይ፤ ጠላቶቼ የሚያደርሱብኝን መከራ ተመልከት፤አይተህም ራራልኝ፤ ከሞት ደጅም አንሥተህ መልሰኝ፤

14. ይህን ስታደርግልኝ፣ በጽዮን ሴት ልጅ ደጅ፣ምስጋናህን ዐውጃለሁ፤በማዳንህም ሐሤት አደርጋለሁ።

15. አሕዛብ በቈፈሩት ጒድጓድ ገቡ፤እግራቸውም ራሳቸው በስውር ባስቀመጡት ወጥመድ ተያዘ።

16. እግዚአብሔር በትክክለኛ ፍርዱ የታወቀ ነው፤ክፉዎችም በእጃቸው ሥራ ተጠመዱ። ሒጋዮን ሴላ

17. ክፉዎች ተመልሰው ወደ ሲኦል ይወርዳሉ፤እግዚአብሔርን የሚዘነጉ ሕዝቦችም ሁሉ እንደዚሁ።

18. ችግረኞች ግን መቼም ቢሆን አይረሱም፤የድኾችም ተስፋ ለዘላለም መና ሆኖ አይቀርም።

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 9