ብሉይ ኪዳን

አዲስ ኪዳን

መዝሙር 89:3-6 መጽሐፍ ቅዱስ፥ አዲሱ መደበኛ ትርጒም (NASV)

3. አንተም እንዲህ ብለሃል፤ “ከመረጥሁት ጋር ኪዳን ገብቻለሁ፤ለባሪያዬ ለዳዊት ምያለሁ፤

4. ‘ዘርህን ለዘላለም እተክላለሁ፤ዙፋንህንም ከትውልድ እስከ ትውልድ አጸናለሁ።’ ” ሴላ

5. እግዚአብሔር ሆይ፤ ሰማያት ድንቅ ሥራህን፣ታማኝነትህንም በቅዱሳን ጉባኤ መካከል ያወድሳሉ፤

6. በላይ በሰማያት ከእግዚአብሔር ጋር ማን ሊስተካከል ይችላል?ከሰማያውያን ፍጥረታትስ መካከል ማን እግዚአብሔርን ይመስለዋል?

ሙሉ ምዕራፍ ማንበብ መዝሙር 89